በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 9 2024 በግሪክ ግሊፋዳ ከተማ የሼፍልድ ዩነይትዱ ተጭዋች ጆርጅ ባልዶክ በመኖሪያ ቤቱ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ሞቶ መገኘቱ ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየው የግሪክ ፖሊስ የተጫዋቹ ህልፈት በድንገት ባጋጠመው የልብ ህመም መነሻነት መሆኑን ይፋ አድርጓል። ባልዶክ በመኖሪያ ቤቱ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ብቻውን የነበረ በመሆኑ ሰው እንዳይደርስለት ምክንያት መሆኑም ተንስቷል።
ፖሊስ ተጫዋቹ አደንዛዥ እጽ ወስዶ ሊሆን ይችላል በሚል የሚሰጠውም አስተያየት ከእውነት የራቀ እንደሆነ እና ምንም አይነት ዕጽ አለመገኘቱን ጠቅሷል። ባልዶክ ላይ ወንጀል መፈጸሙንም የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለመገኘቱንም አያይዞ አንስቷል።
የ31 አመቱ ጆርጅ ባልዶክ በዋና ገንዳ ውስጥ ከሞተበት ዕለት በፊት የልጁን ልደት ለማክበር ወደ እንግሊዝ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበር ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












