በሳዑዲ አረቢያ ፐብሊክ ኢንቨስትመንት ፈንድ ባለቤትነት የሚተዳደረው ኒውካስትል አዲስ የስፖርት ዳይሬክተር ሊሾም ውይይት ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
አዲሱ ተሿሚ እንግሊዛዊው ሮስ ዊልሰን ሲሆኑ ከአሰልጣኝ ኤዲ ሃው ጋር የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው ተብሏል። የ41 አመቱ ዊልሰን አሁን በኖቲንግሃም ፎረስት የአካዳሚው ሃላፊነት ላይ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን በኒውካስትል የቀረበላቸውን የስራ ዕድል ፈቃደኛ ሆነው ይቀበላሉ ተብሎ ይገመታል።
የኒውካስትል ባለቤቶች በባለሙያው ስራዎች ላይ ለረጅም ጊዜ ጥናት በማድረግ ለቦታው ትክክለኛው ሰው መሆናቸውን አረጋግጠዋል ተብሏል። በዘመናዊው እግር ኳስ በተጫዋቾች ምልመላ እና ግዢ በአጠቃላይ በቡድን ውጤት ላይ የስፖርት ዳይሬክተሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ በላፉት አመታት ታይቷል።
ማግፓይሶቹም ከ ፖል ሚሼል መልቀቅ ወዲህ በስፖርት ዳይሬክተርነት ሮስ ዊልሰንን በመቅጠር ክለባቸውን ወደ ዋንጫ አሸነፊነት ለመውሰድ የቆረጡ ይመስላል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












