በሩሲያ 49 ሰዎችን ያሳፈረ ኤንቶኖቭ-24 አውሮፕላን ደብዛው ጠፋ፡፡
በአሙር ግዛት ሲበር የነበረው አውሮፕላን የገባበት አለመታወቁን የሩቅ ምስራቅ ሩሲያዋ ግዛት ገዥ አስታውቀዋል፡፡ እንደ ገዥው ቫሲሊ ኦርሎቭ ንግግር አውሮፕላኑ አምስት ታዳጊዎችን ጨምሮ 43 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከብላጎቪሽንስክ ወደ ቲንዳ እየተጓዘ ነበር፡፡
የ570 ኪ.ሎ ሜትር ጉዞ የማድረግ የበረራ ግዴታ የነበረበት ኤንቶኖቭ -24 በአሙር ግዛት ደብዛው መጥፋቱ አነጋገሪ ሆኗል፡፡ አውሮፕላኑ ከመዳረሻው በርካታ ኪ.ሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከራዳር ስርዓት ውጭ መሆኑም ተወስቷል፡፡
ፍላጋው በአሁኑ ሰዓት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገዥው ዕወቁልን ብለዋል፡፡ አካባቢው በጫካ የተሸፈነ መሆኑ የፍለጋ ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ኤንቶኖቭ An-24 አውሮፕላን በ1950ዎቹ ለጭነት እና ለሰዎች መጓጓዣ በሚል ነበር የተሰራው ፡፡
በአሁኑ ሰዓት አውሮፕላኑ በሩሲያ ምድር ለተወሰኑ የንግድ በረራዎች እንደሚያገለግልም ተነግሯል፡፡ ደብዛው የጠፋው አውሮፕላን በአንጋራ አየር መንገድ ሲደረግ የነበረ በረራ አንዱ አካል ነው፡፡ ከሩቅ ምስራቅ እስከ ምስራቅ ሳይቤሪያ አገልግሎት የሚሰጥ አየር መንገድ መሆኑም ይታዋቃል፡፡
ዘገባው የአር ቲ እና ዋሽንግተን ፖሰት ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












