የስፔን ላሊጋው ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ በዚያው በላሊጋው ለአልሜሪያ የሚጫወተውን የቀኝ መስመር ተከላከይ የግሉ ማድረግ ችሏል።
አልሜሪያ ከቀናት በፊት ከወልቭስ የዝውውር ጥያቄው ቀርቦለት ተጫዋቹ ወደ እንግሊዝ ሊሸኘው የነበረ ቢሆንም፣የተጫዋቹ ፍላጎት የዲዬጎ ሲሚዮኔን ቡድን መቀላቀል ሆኗል። አትሌቲኮ ማድሪድ ለዝውውሩ 15 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣የ5 አመት ውል አስፈርሞታል።
የ22 አመቱ ስፔናዊ ባሳለፍነው የውድድር አመት ለአልሜሪያ በሁሉም ውድድሮች 40 ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት ተሰልፎ 1 ጎል ሲያስቆጥር፣5 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል። አትሌቲ ከአንጋፋው የቀኝ መስመር ተከላካይ ሴዛር አዝብሊክዌታ መልቀቅ በኋላ የነበረበትን ክፍተት መሸፈን ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












