በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ በክረምት ልዩ የመምህራን ትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማስጀመሪያ መርሐግብር እየተከናወነ ይገኛል።
በትምህርት ዘርፍ የሚታየውን ስብራት ለመጠገን እና ጥራትን ለማሳደግ የመምህራንን አቅም የሚያሳድገው የአሰልጣኞች ስልጠና መርሐግብር በትምህርት ሚኒስቴር እና በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት ነው የመክፈቻ መርሐ ግብሩ እየተከናወነ የሚገኘው።
በባለፈው ዓመት ከ60 ሺህ በላይ መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠናን የወሰዱ ሲሆን በዘንድሮው የ2ተኛ ዙር መርሐግብርም 84 ሺህ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው በመድረኩ ተገልጿል።
የትምህርት ዘርፉ ስብራት የቱ ጋር እንደሆነ በመለየት ጥናት እና ምርምር በማድረግ የትምህርት ሂደቱን ከስጋት መታደግ የመርሐ ግብሩ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












