6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባውም የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን የሚያፀድቅ ይሆናል።
የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል መረጃውን ያጋራን ምክር ቤቱ ነው።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












