የጀርመኑ ክለን አር ቢ ላይብዚሽ ከኔዘርላንዱ ፒኤስቪ አይንድሆቨን የክንፍ አጥቂውን ማስፈረም ችሏል።
ላይብዚሽ የ21 አመቱን ቤልጂየማዊ የግሉ ለማድረግ 22 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣እስከ 2030 የሚያቆየውን የ5 አመት ውል አስፈርመውታል። ተጫዋቹ በኖቲንግሃም ፎረስት በጥብቅ ይፈለግ የነበረ በመሆኑ ወደ እንግሊዝ ይጓዛል ቢባል፣ፍላጎቱ የጀርመኑን ቡድን መቀላቀል ሆኗል።
ባካዮኮ ከፊርማ ስነስርዓቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ በመጪዎቹ አምስት አመታት የባላንዶር አሰናፊ መሆን እፈልጋለሁ፣ያንን ለማሳካትም ክለቡ ያግዘኛል ብዬ አምናለሁ”ሲል ተናግሯል። ዮሃን ባካዮኮ በኤርዲቪዜ ቆይታው ለፒኤስቪ በተሰለፈባቸው 130 ጨዋታዎች 33 ግቦችን ሲያስቆጥር፣26 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












