በኢራቅ ኩት ከተማ የገበያ ማእከል ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በርካቶች መሞታቸውን እንዲሁም መቁሰላቸውን ተገለጸ፡፡
የግዛቱ አስተዳዳሪ መሀመድ አል-ሚያሂ እንደተናገሩት የተጎጂዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡ በቃጠሎው ከተጎዱት መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን የገለፁት ኃላፊው ቃጠሎውን ባስነሳው ሰው ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።
ማዕከሉ ከአምስት ቀናት በፊት እንደተከፈተ የተነገረ ሲሆን የቃጠሎው መነሾ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የታወቀ ነገር የለም፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












