የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ታራ ሞር አበረታች መድሃኒት በመውሰድ የ4 አመት እገዳ ተላለፈባት።
እንግሊዛዊቷ ታራ ሞር 18 ወራት ከወሰደ የናሙና ምርመራ በኋላ አበረታች እንክብል መውሰዷ ተረጋግጧል። የ18 ጊዜ የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮኗ 4 አመት ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር የታገደች ሲሆን፣በምርመራ ሂደት ያለፈችበት 18 ወር ተቀናሽ ይሆናል ተብሏል።
ታራ ሞር አሁን ላይ እገዳ የተላለፈባት ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።በግንቦት 2022 በኮሎምቢያ ቦጎታ በተደረገው የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና በተመሳሳይ አበረታች መድሃኒት በመውሰድ ቅጣት ተላልፎባታል።
በሚያዚያ 2024 ወደ ስፖርቱ ስትመለስ አሁን ላይ ቅጣት እስኪገጥማት ድረስ የአለማቀፍ ቴኒስ ፌዴሽን (ITF) በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ስትካፈል ቆይታለች።
የ32 አመት ስፖርተኛዋ አሁን ላይ በገጠማት ዕገዳ እስከ አውሮፓውያኑ 2028 ወደ ሜዳ የማትመለስ መሆኑ ከዕድሜዋ መግፋት ጋር ተያይዞ እስከ መጨረሻው ልትሰናበት እንደምትችል ተገምቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












