የ2017 የ12 ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን በማስመልከት ትምህርት ሚኒስቴር ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በመጣመር መግለጫ ሰጥቷል።
የዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከዚህ በፊት ከነበሩት ዓመታት በተሻለ ሰላማዊ፣ ስርቆት የቀነሰበት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል። በተሰሩ ስራዎች የፈተና ስርቆት በመቀነስ ተማሪዎች በራሳቸው መስራትን ባህል እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
የተማሪዎች ዝግጅት፣የመምህራኑ እና የወላጅ ቁጥጥር በመጨመሩ ከባለፈው ዓመት በተሻለ ውጤት ሊመዘገብ እንደሚችል ተናግረዋል።
ፈተናው ከወሰዱ 581 ሺህ 905 ተማሪዎች 134 ሺህ 828 ተማሪዎች በበይነመረብ በመፈተናቸው ከባለፈው ዓመት አንጻር 4 እጥፍ ማሳደግ መቻሉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በፈተናው ወቅት ካጋጠሙ ችግሮች አምስት ቀላል የትራፊክ አደጋ ተከስቷል ሆኖም በመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አግኝተው ፈተናቸው ላይ መቀመጥ መቻላቸውን ተጠቁሟል
በ ሰላም ይልማ












