በአሜሪካ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የክለቦች አለም ዋንጫ በእንግሊዙ ቼልሲ ሻምፒዮንነት መጠናቀቁ ይታወሳል።
በአዲስ ቅርጽ ውድድሩን ያዘጋጀው የአለማቀፉ የእግርኳስ ማህበር ፊፋ አስደናቂ ችሎታ ያሳዩ 11 ተጫዋቾችን ስም ይፋ አድርጓል። የውድድሩ አሸናፊ ቼልሲ 4 ተጫዋቾችን ማስመረጥ የቻለ ሲሆን፣ፊፋም ለመረጣቸው ተጫዋቾች የ4-4-2 አስተላለፍ ሰርቷል።
በግብ ጠባቂነት የሳዑዲው ክለብ አል ሂላል ተጫዋች የሆነው ያሲን ቦኖ ተመርጧል። የ34 አመቱ ግብ ጠባቂ ከምድብ ድልድል እስከ ሩብ ፍጻሜው በተጓዘው ቡድን ውጤታማ እንቅስቃሴ አሳይቷል።
በተከላካል መስመር የፒኤስጂዎቹ አሽራፍ ሃኪሚ እና ማርኪኒዮስ፣ የፓልሜራሱ ቲያጎ ሲልቫ እና ከሻምፒዮኑ ቼልሲ ኩኩሬላ ተካተዋል። ሃኪሚ እና ማርኪኒዮስ እስከ ፍጻሜ በደረሰው ፒኤስጂ ተደናቂ ብቃት ማሳየት የቻሉ ሲሆን፣የ40 አመቱ አንጋፋ ቲያጎ ሲልቫም እስከ ግማሽ ፍጻሜ በደረሰው ቡድኑ ሞገስን አግኝቷል።
በአማካኝ መስመር ፔድሮ ኔቶ፣ቪቲኒሃ፣ኤንዞ ፈርናንዴዝ እና ኮል ፓልመር መግባት ችለዋል። የፊት መስመሩን የፓልሜራሱ ጄሱስ አሪያስ እና የሪያል ማድሪዱ ወጣት አጥቂ ጎንዛሎ ጋርሺያ ይመሩታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












