የካታላኑ ኤስፓኞል በአሜሪካዊው ባለሃብት አለን ፔስ ድርጅት velocity sport limited በ180 ሚሊየን ዩሮ ከፍተኛው ድርሻ መገዛቱን ክለቡ አስታውቋል።
አለን ፔስ በንግድ ስራ ስማቸው የናኘ፣ የእንግሊዙ በርንሌይም ባለቤት እና ዋና ስራ አስፈጻሚ መሆናቸው ይታወቃል። በርንሌይ እና ኤስፓኞል በስፖርታዊ ጉዳዮች ከዚህ በኋላ አብረው ይሰራሉም ተብሏል።
ኤስፓኞል በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከላሊጋው የመውረድ ስጋት ውስጥ የነበረ ሲሆን፣መትረፉን ያወቀው በመጨረሻው ሳምንት ሪያል ቫላዶሊድን በማሸነፍ ነበር። በርንሌይ በአለን ፔስ ባለቤትነት ከተያዘ ወዲህ ከፕሪምየር ሊግ ሁለት ጊዜ ቢወርድም ተመልሶ መምጣት ችሏል።
በአሰልጣኝ ስኮት ፓርከር የሚሰለጥነው በርንሌይ በ2025-26 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከቶተንሃም ሆትስፐር የሚያደርግ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












