የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልጸው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ ዘንድሮም ከአምናው የተሻለ ውጤት ለመመዝገብ ችላል ብለዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን ጠቁመው ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ውጤቱም ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 70,525 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡












