::::::::::::::::::::::::::::::::::
ውድድሮች ዛሬ ከጠዋቱ 2:00 አንስቶ በብስክሌት፡ በባድሚንተን፣በጅምናስቲክ ፣ በእግር ኳስ፣ በዉሃ ዋና፣ በጠረጴዛ ቴኒስ እና በእጅ ኳስ በሁለቱም ጾታ በመካሄድ ላይ ነው።
በባድሚንተን ውድድር ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ከተማን አሸንፏል። በሴቶች እግር ኳስ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን 2-0 ድል ማድረግ ችሏል።

በተመሳሳይ በሴቶች እግር ኳስ ጋምቤላ ክልል ከአማራ ክልል የሚያደርጉት ጨዋታ በመከናወን ላይ ሲሆን የጋምቤላ ክልል ጨዋታወን 1-0 እየመራ ይገኛል።
በወንዶች እግር ኳስ ደቡብ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል እንዲሁም አፋር ክልል ከ ሶማሌ ክልል ከቀኑ 8:00 ሰዓት እና 10:00 ሰዓት በጅማ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በ- ይበልጣል ሰውነት ከጅማ












