
የኢራኑ ሁለንተናዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን እንደገለፁትም “አሜሪካውያን እና የዚህን ክልል ፖለቲካ ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ተሳትፎ ጉዳት እንደሚያደርስ ያውቃሉ” ብለዋል።
አሜሪካ ከዚህ የእስራኤል ጥፋት ጋር የምትተባበር ከሆነ ከባድ የሆነ አደጋ በቀጠናው ይደርሳል ሲሉ የትራምፕን መንግስት አስጠንቅቀዋል የኢራኑ ሁለተናዊ መሪ።
ኻሚኒ አክለውም፣ በኢራን ላይ ሊደርስ ከሚችለው ከማንኛውም ጉዳት የበለጠ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን አሣስበዋል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከኢራን ውስጥ ዘገባ ማቅረብ አይችሉም። ስለዚህ የሳተላይት ምስሎች በመጠቀም የእስራኤል ጥቃት ያስከተለውን ጉዳት ለማየት እና ለማረጋገጥ ቁልፍ መሳሪያ ሆኗል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
በደረሰው ጉዳትም ቢያንስ ዘጠኝ ህንፃዎች፣ የአውሮፕላን ጣቢያዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን የሳተላይት ምስሎቹ አሣይተዋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው
በ – ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












