የቀድሞው ኮከብ ሙሉጌታ ከሳምንታት የህክምና ዕርዳታ በኋላ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል።
ዛሬ ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሽን ባለስልጣናት፣የተጫዋቹ ወዳጅ ዘምድ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሽኝት ስነስርዓት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ የአበባ ጉንጉን ካሳረፉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ሙሉጌታ ከበደ “ወሎዬው” ያልሸነፍ ባይነት ምልክት ነው ብለዋል።
አያይዘውም ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ያስጠራ፣ለተጫዋቾች መልካም ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የቀድሞው ኮከብ ሙሉጌታ ከበደ የቀብር ስነስርዓት በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ከቀኑ 7 ሰዓት እንደሚፈጸም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












