::::::::::::::::::::::::::::::::
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው ተስፋዬ ነዋይን የኢትዩጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል።
ተሿሚው ተስፈዬ ነዋይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፥ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎችም ያገለገሉ ናቸው።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር ቦርድ አባላትን ሹመት ያጸደቀ ሲሆን፥ በዚህም ተክሊት ይምሰል እና ነሲብ ዐሊ የቦርዱ አመራሮች በመሆን ተሹመዋል።
ተክሊት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆኑ፥ በነሲም አሊ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ተሿሚዎቹ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል።ሹመቱ በሁለት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን












