። ። ። ። ። ። ። ። ።
የደቡብ ለንደኑ ክለብ ክሪስታል ፓላስ፣ በኤፍ ኤካፕ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲን በማሸነፍ በቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ውድድር ተሳትፎን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘቱ ይታወሳል።
በክለቡ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነት መገኘቱ ከፍ ያለ ጉጉት መፍጠር ቢችልም፣ አሁን ላይ ደስታቸውን የሚያጨልም ጉዳይ ተከስቷል።
በዩኤፋ ደንብ መሰረት በአውሮፓ ውድድር የሚሳተፉ ክለቦችን ባለቤትነት በተመለከተ በተመሳሳይ ባለሃብት የሚተዳደሩ ክለቦች በአንድ የውድድር መስክ እንዲሳተፉ አይፈቀድም።
የክሪስታል ፓላስ ባለቤት ዴቪድ ቢልዘር የፈረንሳዩ ሊዮንም ንብረታቸው ስለሆነ ከሁለት አንዱ ቡድን ከቀጣይ ዓመት የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነት መቀነሱ የግድ ነው ተብሏል።
አሜሪካዊው ባለሃብት በእንግሊዙ ክለብ የ25 በመቶ ድርሻ ያላቸው ሲሆን፣ ሙሉ ባለቤትነት የላቸውም በሚል ክሪስታል ፓላስ ለዩኤፍኤው ይግባኝ ማለቱ ተሰምቷል።
ዩኤፋ በቀጣዮቹ ቀናት ይግባኙን ተመልክቶ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ተዘግቧል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












