::::::::::::::::::::::::::::::
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ከሚወስዱት 600ሺ ተማሪዎች ውስጥ 150 ሺ የሚሆኑት በበይነ መረብ ይፈተናሉ ሲሉ የትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።
ሀገራዊ ፈተናውን ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉም ፕሮፌሰር ብርሀኑ አስታውቀዋል።
ከባለፈው ዓመት በተሻለ 150 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎች ፈተናቸውን በበየነ መረብ ይወስዳሉ ያሉት ሚኒስትሩ፣ በዚህ ሂደት በቀጣይ ሶስት ዓመታት ሁሉም ተማሪዎች በበየነ መረብ የሚፈተኑበት ሁኔታ ይፈጠራል ነው ያሉት።
የፈተና አስተዳደር ሥርዓቱ በዚህ መልኩ መስመር ከያዘ ብቃት ያላቸውና ተወዳድሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለማፍራት ይቻላል ብለዋል።
አክለውም የትምህርት ጥራት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራት ላይም ርብርብ ይደረጋል ማለታቸውን ሚንስትር መ/ቤቱ ይፋዊ ገጽ አስታውቋል።
በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች በወረቀትና በበየነ መረብ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።












