እንግሊዛዊው አማካኝ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ምሽት በይሮፓ ሊግ ቦዶ ግሊምትን ከሚገጥምበት ጨዋታ አስቀድሞ ከአሰልጣኙ ጋር በጋራ መግለጫ ሰጥቷል።
ቶተንሃም ሆትስፐር በፕሪምየር ሊጉ 37 ነጥብ በመያዝ 16ተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጦ፣ በታሪኩ እጅግ ደካማ የተባለውን የውድድር እያሳለፈ ይገኛል።

አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ ስራቸውን ለማዳን ክለቡን በይሮፓ ሊግ ሻምፒዮን አድርገው፣ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነትን በአቋራጭ ማሳካት ግዴታ ተደርጎባቸዋል ቢባልም፣ በውድድር አመቱ በጨረሻ መሰናበታቸው አይቀሬ ነው ተብሏል።
በክለቡ ውጤት የጠፋው ከተጫዋቾቻቸው ጋር አለመግባባት ተከስቶ ሊሆን ይችላል በሚል አማካኙን ማዲሰን በጋዜጠኞች ተጠይቋል።
ማዲሰን “የመልበሻ ክፍሉ መቶ በመቶ ከአሰልጣኙ ጎን ነው፣ ትልቅ አሰልጣኝ ነው፣የሚሰጠንን የጨዋታ ስልጠና ተግባራዊ ለማድረግ ሁሌም ፈቃደኞች ነን” ብሏል።

አክሎም ”በፕሪምየር ሊግ ደካማ የውድድር አመት እያሳለፍን ነው፣ አሁን በእጃችን ያለውን የይሮፓ ሊግ እድል መጠቀም ይኖርብናል” ሲል ተናግሯል።
ቶተንሃም ሆትስፐር ምንም አይነት ዋንጫ አሸናፊ ከሆነ 17 አመት ተቆጥሯል። ምሽት በሜዳው የሚያስተናግደው የኖርዌዩ ቦዶ ግሊምትን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገጥም ይሆናል።
ቦዶ የጣሊያኑን ላዚዮ በመለያ ምት አሸንፎ፣ቶተንሃምም የጀርመኑን ሊቨርኩሰንን በመጣል ነበር ለግማሽ ፍጻሜ የደርሱት።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












