።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሜሪካ ታሪካዊ የተባለለትን “የብርቅዬ ተፈጥሮ ማዕድናት” ስምምነት ከዩክሬን ጋር መፈራረሟ ተገለፀ።
ኬይቭና ዋሺንግተን ወራትን ከተሻገረ ውይይት በኋላ በስተመጨረሻ አሜሪካ ከዩክሬን ብርቅዬ ማዕድናት ማግኘት የምትችልበትን ፊርማ አኑረዋል።
“የዳግም ግንባታ ኢንቨስትመንት ድጋፍ” በሚል ስያሜ ስር ሀገራቱ ፊርማቸውን ማኖራቸው በጋዜጣዊ መግለጫው ተነስቷል።
ስምምነቱ የሀገራቲን የጋራ ተጠቃሚነትና አቅምን ያጠናክራል ለኬቭ ማገገም ወሳኝ ነውም ተብሎለታል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ500 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ማዕድን በካሳ መልክ ከዩክሬን እንደሚሹ ደጋግመው ሲገልፁ ከርመዋል።
ባሳለፍነው ወርሀ የካቲት የስምምነቱን የተወሰነ ክፍል መሄድ ተችሎም ነበር።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ለስምምነቱ እውናዊነትና ለበርካታ ጉዳዮች ወደ ነጩ ቤተመንግስት ተጉዘው ያልጠበቁት አስደንጋጭ አቀባበልና ከትራምፕ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ስምምነቱ ውድቅ ሆኖ ቆይቷል።

ከወራት ውይይትና ንግግር በኋላም ታዲያ ታሪካዊው ስምምነት ተፈፅሟል።
ስምምነቱ አሜሪካን እንደ አልሙኒየም, ግራፉይት, ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቶችን ከዩክሬን እንድታገኝ ያስችላታልም ተብሏል።
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ አሜሪካ የገፈገፈችውን ቢሊየን ዶላሮች ለመመለስ የማዕድን ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑን ዶናልድ ትራምፕ ከስምምነቱ በኋላ አንስተዋል።
ዘገባው የቢቢሲና ሮይተርስ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












