፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በዚህች ቀን የዛሬ 113 ዓመታት የዩናይትድ ኪንግደም ታላቋ መርከብ ከበረዶ አለት (ግግር) ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ታይታኒክ መርከብ የመስጠም አደጋ አጋጥሟት 1500 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
ከጊዜ ወዲህ የወጡ ጥናቶች ደግሞ ከመርከቧ ክፍል እሳት ተነስቶ ነው የሚል መንስኤን አስቀምጠዋል።
ያም ሆነ ይህ መርከቧ ከሳውዝሃምፕተን እንግሊዝ ተነስታ ወደኒውዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ስታቀና ነበር አደጋው ያጋጠማት።
269 ሜትር ርዝመት እና 28 ሜትር ስፋት የነበራት በታሪክ ዝነኛዋ መርከብ ታይታኒክ በዋይት ስታር ላይን ካምፓኒ የተሰራች ሲሆን ደብዛዋ ጠፍቶ ፈልጎ ለማግኘት 73 ዓመታት ያህል ፈጅቷል።
ከመሬት ጥልቀት 3800 ሜትር ስር መርከቧ ተገኝታም ተመራማሪዎች በየጊዜው ጥናት እና መላምታቸውን ሲያስቀምጡ ነበር።
በ2030 ምንም አይነት ቁሳዊ ቅሪት አይኖራትም የሚለውም አንደኛው ምርምር ነው።
በታይታኒክ መርከብ ከነበሩ ከ2240 የታይታኒክ ተሳፋሪዎች መካከል በፊልም ጭምር የተሰራውን የጃክ እና ሮዝን ታሪክ የሚያስታውሱት ብዙዎች ናቸው።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ












