የ44 ዓመቱ ቤናዮን “በስህተት” የተባለው ጥቃት በተሰነዘረ ጊዜ በሰሜናዊ ቴል አቪቭ በራማት ሀሻሮን በሚገኘው ቤቱ ውስጥ እንደነበር ዘ ሰን ዘግቧል።
ፈንጁን አንድ ሞተር ሳይክል ነጂ በሩ ላይ እንደወረወረው ዘገባው አክሏል።ጥቃት ፈጻሚው እንዳመለጠና የተጎዳ ሰው እንደሌለም ተመላክቷል።
የአካባቢው የፖሊስ ሃይሎች አሁንም ምርመራ እያደረጉ ሲሆን ክስተቱ እንደ ሽብር ሳይሆን እንደ ወንጀል ይቆጠራል ብለዋል።
በዌስትሃምና አርሰናል ክለቦች ጭምር ተጫውቶ ያሳለፈው ዮሲ ቤናዮን በበኩሉ ጥቃቱ እርሱንና ቤቱን ኢላማ ያደረገ እንዳልነበረ ይልቁንም በስህተት እንደተፈጸመ ተናግሯል።
በ-ይበልጣል ሰውነት












