::::::::::::::::::::::
በአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የተቋም ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ በክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በማተኮር ምክክር እንደሚደረግ ተገልጿል።
በተጨማሪም በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።












