፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ቼልሲ በለንደን ደርቢ ቶተንሃምን ከሚያስተናግድበት ጨዋታ አስቀድሞ አሰልጣኙ የሳንቾን ቆይታ በሚመለከት አስተያየት ሰጥተዋል።
ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ውል በምዕራብ ለንደኑ ክለብ የሚገኘው ጄደን ሳንቾ በውድድር አመቱ በ29 ጨዋታዎች 2 ግቦችን ብቻ አስቆጥሯል።
ቼልሲ ተጫዋቹን በውድድር አመቱ መጨረሻ በ 25 ሚሊዮን ፓውንድ በቋሚነት የማስፈረም ስምምነት ያለው ሲሆን ተጫዋቹን ወዳዋሰው ክለብ የሚመልስ ከሆነ 5 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲከፍል ይገደዳል።
ተጫዋቹን በቋሚነት ስለማስፈረም የተጠየቁት ማሬስካ “ትኩረቴ በሚቀሩን ጨዋታዎች ላይ ነው፣ስለሳንቾ ዝውውር ለመናገር ጊዜው አይደለም “ብለዋል።
የክለቡ የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት ከሆነ ሰማያዊዎቹ የ25 አመቱን እንግሊዛዊ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለመመለስ ተዘጋጅተዋል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ











