የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የወጣት ሚኒስትሮችና አመራሮች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት ፉአድ ገና አቀባበል አድርገውላቸዋል።
እንግዶቹ የጅቡቲ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኬንያ፣ የአልጄሪያ፣ የብሩንዲ እና የጋቦን ተወካዮች መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።











