፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 08 2017| NBC ETHIOPIA- በፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር) እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር ) የተመራው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢ የተገነባውን የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሐም ታደሰ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃይለማርያም የኮሪደር ልማቱንና የተጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ለሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት አስጎብኝተዋል።

የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራው ሲጠናቀቅ የወንዙን ሕልውና በመታደግና የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ነፋሻማና ለመኖሪያ ምቹ አካባቢን እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

በተመሳሳይም አራት ኪሎ ፕላዛ የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገድና ከአራት ኪሎ ፒያሳ መሀል የሚገኘው የራስ መኮንን የመስታወት ድልድይ ግንባታ ስራ ለከተማዋ ደረጃ የሚመጥን በመሆኑ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ሱፐርቪዥን ቡድኑ መግለጹን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።












