፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 27 2017| NBC ETHIOPIA-“ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል የነገ ስብዕናን ይገነባል” በሚል መሪ ቃል ላለፈው አንድ ወር በተለያዩ ተግባራት ሲከበር የቆየው የፀረ-ሙስና ወር አካል የሆነ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
“ስነ-ምግባራዊ ትውልድ ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የአዲስ አበባ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት መድረኩ ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ እየተደረገ የሚገኘውን ጥረት ለማገዝ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ምህረቱ ሻንቆ (ዶ/ር) ለሙስና ምክንያት የሆኑ በርካታ ጉዳዮች ስለመኖራቸው እና ስራ አጥነት አንዱና ዋነኛው ስለመሆኑ አብራርተዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመግታት የስራ እድል ፈጠራ ሊጠናክር እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሙስና የዜጎችን ነፃነት የሚያሳጣ፣ ፍትህን የሚያዛባ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማል ረዲ በበኩላቸው ወጣቱ ችግሩን ለመዋጋት ወሳኝ ስለመሆኑ ገልፀዋል። ይህንንም ተከትሎ እንደ ከተማ እየተደረገ ያለው ችግሩን የመዋጋት ትግል አካል እንዲሆን የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

የፀረ-ሙስና ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/












