፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 30 2017| NBC ETHIOPIA- ስፔስ ኤክስ (SpaceX) 23 የስታርሊንክ ሳተላይቶችን ከፍሎሪዳ ኬፕ ካናቨራል የጠፈር ኃይል ጣቢያ አመጠቀ።
“ፋልከን 9” ተብሎ በሚጠራው የስፔስ ኤክስ መንኮራኩር የመጠቁት ሳተላይቶቹ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ምህዋራቸው የተሰማሩ ሲሆን ከእነዚህ ሳተላይቶች 13ቱ ከስማርት ሞባይሎች ጋረ ቀጥታ ግንኙነት ይኖራቸዋል።

የአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢላን መስክ ድርጅት የሆነው ስታርሊንክ በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ዝቅተኛው የምድር ምህዋር (Low Earth Orbit) በማምጠቅ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ፈጣን ኢንተርኔት ለተጠቀሚዎች ማቅረብን አላማው አድርጎ የተመሰረተ ድርጅት ነው።

ስፔስ ኤክስ በ2024 ውስጥ ከ80 በላይ የስታርሊንክ ተልእኮዎችን የፈጸመ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከ6800 በላይ ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የስታርሊንክ ሳተላይቶች በዝቅተኛው የምድር ምህዋር ላይ ይገኛሉ።
ኢላን መስክ በኤክስ ገጹ እንደገለጸው የመጀመሪያው የስታርሊንክ ከሳተላይት ወደ ስልክ ቀጥታ ግንኙነት መፍጠር የሚያስችል የሳተላያቶች ስብስብ የተሟላ ሲሆን ይህም ኢንተርኔት በቀላሉ በማይገኝባቸው አካባቢዎች ስልኮች በሞገድ 10 ሜጋባይት በሚደርስ ፍጥነት ኢንተርኔት እንዲጠቀሙ ያስችላል።ዘገባው የዩፒአይ ነው።
በ- ዳንኤል መኮንን











