የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁርካ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ አሻራ አበታች ውጤት መመዝገቡን አንስተው ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የግብርና ሜካናይዜሽን ጉዳዮች ላይ ከቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት ገልፀዋል፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁርካ በበኩላቸው በኢትዮጵያ መንግስት እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ስራዎችን አድንቀው በግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦት እና በእንስሳት ልማት ላይ በትብብር ለመስራት ቼክ ሪፐብሊክ ያላትን ቁርጠኝነት አሳይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተመራው የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ጊቢ ያሉ የእርሻ መሳያዎች፣ ትራክተሮችን እና የመገጣጠሚያ ማዕከላት መመልከታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።












