፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ከሰማንያ በመቶ በላይ የጀርመን ወጣቶች በአውሮፓ አህጉር ግዙፍ ጦርነት ይካሄዳል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው አንድ ጥናት ገልጿል።
በጀርመን ወጣቶች ዘንድ የአውሮፓን ግዙፍ ጦርነት ስጋት ያናረው ነገር በዋናነት በአህጉሩ ምስራቃዊ ክፍል እየተካሄደ ያለው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ የከፋው የአየር ንብረት ለውጡ ጫናና የፖለቲካው ትኩሳት መሆኑም ነው የተገለጸው።
የአውሮፓ አህጉር የጦርነት ስጋት በመንስኤነት የከፋ ድህነት በብዙዎቹ ሀገራት ዘንድ እየተስፋፋ መታየቱ መሆኑን ከዚያም በላይ በሩሲያና ዩክሬን መካከል ጦርነቱ የመስፋፋቱና ሀማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት የጦርነትን አይቀሬነት አመልካች ነው ሲል የኪቭ ኢንዲፔንደንት ዘገባ ያስረዳል።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












