፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 05 2017| NBC ETHIOPIA- የትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የማለፊያ ውጤትን ይፋ አድርጓል።
1. የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከስድስት መቶ 192፣
2. የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከስድስት መቶ 186፣
3. በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ወንድ ከሰባት መቶ 224፣ እና
4. በፕሪፓቶሪ ፕሮግራም የተፈጥሮ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ሴት ከሰባት መቶ 217 እና በላይ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡












