፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 01 2017| NBC ETHIOPIA-የኢሚግሬሽንና ዜግነት አልገልግሎት የበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት አፈጻጸሙን ሪፖርት አቅርቧል፡፡
በሩብ ዓመቱ 367 ሺህ ፓስፓርት ታትሞ ለደንበኞች መሰራጨቱን አገልግሎቱ አስታውቋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አልገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ከነሀሴ 1 2016 ዓ.ም ጀምሮ የክፍያ ማሻሻይ ያደረገው ተቋሙ በአስቸኳይ የፓስፖርት አሰጣጥ ረገድ ከ22 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ፓስፖርት ፈላጊዎች አግልግሎት ሰጥቷል ብለዋል።

አገልግሎቱ በአሰራሩ ላይ የሚታዩ ክፍትቶችን ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሰላማዊት ዳዊት በኦላይን አገልግሎት የመስጠት አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በ2025 መጀመሪው ወር ስራውን ይጀምራል ተብሏል።የፓስፖርት አገልግሎት ግዜ ገደብን 10 ዓመት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












