ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
በ2017 በጀት ዓመት የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችን አቅም በየጊዜው በመገንባት ህገ-ወጥ ተግባራትን የመከላከል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

የጽ/ቤቱ የስራዎች አስተባባሪ ሙሉቀን እንየው እንደተናገሩት የኦፊሰሮችን አቅም በየጊዜው በመገንባት ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል አቅም እንፈጥራለን ብለው ስልጠናው በ3 ዙሮች እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
አስተባባሪው አክለውም ስልጠናዎቹ የኦፊሰሮችን አቅም በማሳደግ ህገ-ወጥ ተግባራትን በተደራጀ መንገድ ለመከላከል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡












