፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 02 2017| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚያከናውነው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ምክንያት የጥሪ ማዕከሎቹ አገልግሎት እንደማይሰጡ አስታወቀ ፡፡
አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋሩት መልዕክት ከዛሬ ጥቅምት 02 ከቀኑ 6፡00 እስከ ነገ እሁድ ጥቅምት 03 ለሊት 6፡00 ድረስ የሲስተም ማሻሻያ ስራ ስለሚያከናውን 905 እና 904 ነጻ የጥሪ ማዕከሎች አገልግሎት እንደማይሰጡ ገልጿል፡፡

ስለሆነም የሲስተም ማሻሻያ ስራው ተከናውኖ የጥሪ ማዕከሎቹ ወደ አገልግሎት እስኪመለሱ ድረስ የአስቸኳይ ጥገና አገልግሎት የሚፈልጉ ደንበኞች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ወይም በቀጥታ ስልክ በመደወል አገልግሎት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












