፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2017| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል በዓልን በተመለከተ ሲምፓዚያም እያካሄደ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር በድምቀት ሲከበር የቆየው የመስቀል ደመራ በዓል ፤ ኢትዮጵያዊነቱ ጐልቶ የሚታይበት በመሆኑና ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር የሀይማኖት አባቶች ፣አባ ገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎችና ወጣቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።

በመድረኩ መነሻ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች እና ወጣቶች እየተሳተፉበት ይገኛል።
በ-ሀሴት ኃይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












