፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 14 2017| NBC ETHIOPIA-ኩባንያው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙትን የኮፐር መስመሮች ወደ ፍይበር በመቀየር ዘመናዊ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት እና በዳታ ላይ የተመሠረተ የድምፅ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ኮፐር ስዊች ኦፎ የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው የፋይበር መስመር ፈጣን እና አስተማማኝ አግልግሎት መስጠት የሚያስችል ስለመሆኑ ተገልፃል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኢንተርኔት ፍላጎት ተከትሎ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈታ መሆኑ ተነግሯል።
የፋይበር መሥመር አገልግሎት መጀመር ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ አስተዋፆ የጎላ ስለመሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት ከመቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል ።
በ -ሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












