Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

ቦብ ማርሌይ

September 24, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የሬጌው ንጉስ ሲል ዓለም በአንድ ድምጽ ይስማማበታል  በሙዚቃው የሰላምን ዋጋ አስረድቶ አቀንቅኖ የተጣሉትን አስታርቋል፡፡   

ጭቆናን በሚተቹ እና አንድነትን በሚሰብኩ ዘፈኖቹ ዝናና ተወዳጅነትንም አትርፏል፡፡ ታላቁ የሬጌ አቀንቃኝ፣ ሙዚቀኛ እና አቀናባሪ ሮበርት ኔስታ ማርሊ ወይም ቦብ ማርሌይ፡፡

የሬጌ ሙዚቃን በመጫወትና ለሕዝቡ እንዲደርስ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገው ቦብ የሬጌ ሙዚቃ ፈር ቀዳጅና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እንዲሆን ካደረጉት መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል ፡፡

ከዚህ ዓለም በለጋ እድሜው የተለየው ቦብ እ.ኤ.አ በ1980 በትላንትናው እለት ነበር የመጨረሻ ኮንሰርቱን ለአድናቂዎቹ ያደረሰው፡፡ በወቅቱ በአውሮፓ የተዘጋጀ ትልቅ ኮንሰርት ነበር ፡፡

ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ የተወለደው ቦብ ህይወቱን ለማሸነፍ መጣር የጀመረው ገና በልጅነቱ ነበር ፡፡  የሙዚቃ ሕይወቱንም ሀ ብሎ  የጀመረው በ1960ዎቹ መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ ታሪኩ ያወሳል ፡፡ Judge Not የተሰኘው ዘፈኑ የመጀመሪያ ስራው ነው ፡፡ 

ቦብ በ17 አመቱ ፒተር ቶሽ እና በኒ ዌይለር ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር በመሆን ዘ ዌይለርስ የተባለ ቡድን በመመስረት ዘፈኖችን ለአድማጭ ማድረሱን ቀጠለ ፡፡ ነገር ግን ብዙም እንዳልተደመጠ ይነገራል ፡፡

በዚህ ተስፋ ያልቆረጠው ቦብ ማርሌይ በ1975 የለቀቀው No Woman, No Cry የተሰኘ ስራው ከጃማይካ ውጪ በከፍተኛ ደረጃ በመደመጥ ቻለ ፡፡ በመቀጠልም  Rasta man Vibration የተሰኘ ሌላ ስራን በመልቀቅ የቢልቦርድ ሰንጠረዥን በመያዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ማግኘት ችሏል ፡፡

13 የስቲዲዮ አልበሞች ፣ ስድስት Live አልበሞች እና 133 ነጠላ ዜማዎች እና የሌሎች ስራዎች ባለቤት ነው ፡፡ በመላው ዓለም እየተዛወረም በርካታ አድናቂዎቹ በተገኙበት የኮንሰርት ስራዎቹን አቅርቧል ፡፡

በሚሰራቸው  ተሰምተው የማይጠገቡ ስራዎቹ ዝናው እየናኘ የመጣው ቦብ 1976 በትውልድ ሀገሩ ጃማይካ የተቀጣጠለውን የፖለቲካ ግጭት ለማብረድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተዘጋጀ Smile Jamaica በተሰኘ ኮንሰርት ላይ ለመዝፈን ሁለት ቀን ሲቀረው በተቃዋሚዎች እሱ ፣ ባለቤቱ ሪታ ማርሌ እና ማናጀሩ ላይ ጥቃት አድረሰውባቸው ነበር ፡፡ 

ይህም ለቦብ ከሀገሩ መሰደድ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል ፡፡ ወደ ለንደን በማቅናትም ታይም መጽሄት የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጡ አልበም ያለውን Exodus የተሰኘ ስራውን ለአድናቂዎቹ አድርሷል፡፡  

ከሙዚቃ በተጨማሪ የስፖርት እንቅስቃሴ እንደሚያዝናናው የሚናገረው ቦብ  እግር ኳስ ሲጫወት እግሩ ላይ የደረሰበት ጉዳት ወደ ካንሰርነት ተቀይሮም ነበር፡፡

በወቅቱም አውራ ጣቱ እንዲቆረጥ ሀኪሞች ቢመክሩትም የሚከተለው ሀይማኖት እና የራስ ተፈሪያን ሥርዓቱ ባለመፍቀዱ የሀኪሞቹን ሀሳብ ሳይቀበል ቀረ ፡፡

ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ህመሙ እየተባበሰ ቢመጣም በ1980 Uprising የተሰኘ አልበሙን በማስመልከት በተለያዩ ሀገራት እየተዛወረ ስራዎቹን ማቅረብ ጀመረ ፡፡ በሲዊዘርላድ የጀመረው ኮንሰርቱ እ.ኤ.አ 1980 በትላንትናው እለት በPittsburgh ፍጻሜውን አገኘ ፡፡  ከዚህ ኮንሰርት በኋላ ቦብ የቆየው ለወራት ብቻ ነበር ፡፡

በተለያዩ ሀገራት ህክምናውን ሲከታተል የቆየው ቦብ በ1981 በ36 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ፡፡

ህይወቱ ካለፈ በኋላ የተለቀቀው Legend የተሰኘ ስራው በመላው አለም  ከ12 በላይ ቅጂዎቸ በመሸጣቸው የምንግዜውም ምርጥ የሬጌ አልበም መሆን ችሏል፡፡
ፎርብስ መጽሄት በህይወት ሳይኖሩ ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ ሰዎች መካከል አካቶታል ፡፡

ቦብ ማርሌይ በጥቂት እድሜው የሰራቸው በርካታ ሙዚቃዎች አብዛኞቹ በጥቁር መብት እና በአፍሪካ ፖለቲካ ላይ ያጠነጠኑ ናቸው ፡፡

ቦብ ማርሌይ ስለአንድነት፣ ስለሰዎች እኩልነት፣ ስለዓለም ሰላም በማቀንቀን መልካም አስተሳሰብን የሚዘክሩ ጠንካራ ሐሳቦችን በሬጌ የሙዚቃ ሥልት አዋዝቶ ለሕዝቡ በማቅረብ ትልቅ ሥራዎችን ሠርተው ካለፉ  ዘፋኞች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው ፡፡

በ70ዎቹ እና በ80ዎቹ ብቅ ብሎ አሁንም ድረስ በሰዎች ልብ ውስጥ ስላለው ዘመን አይሽሬው ቦብ ማርሌይ የመጨረሻ ኮንሰርቱን ያቀረበበትን ቀን እንዲህ አስታወስናችሁ፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

ኢትዮ ቴሌኮም “ኮፐር ስዊች ኦፍ ” የተሰኘ ኢኒሼቲቭ ይፋ አደረገ

Next Post

ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት

ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅት

 በአማራ ክልል ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ  የሩዝ  ምርት ይጠበቃል  

 በአማራ ክልል ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ  የሩዝ  ምርት ይጠበቃል  

የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?