፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 13 2017| NBC ETHIOPIA- በቀዳማይ ልጅነት ላይ የተለያዩ ስራዎችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፀዉ የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል በተለዋዋጭ የአየር ንብረት ለቀዳማይ ልጅነት መሠረት መጣል በሚል ሃሳብ በአየር ንብረት ለዉጥ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት አካሂዷል።

ከአየር ንብረት ለዉጥ ጋር ተያይዘዉ የሚከሰቱ ችግሮች በቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ ከባድ ስለመሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
ከአየር ንብረት ለዉጥ ጋር ተያይዘዉ የሚመጡ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ለልጆች የሚመች ከባቢን መፍጠር ተገቢ በመሆኑ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በ-ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












