፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 06 2017| NBC ETHIOPIA- የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ ትራምፕ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን አስቆመዋለሁ ማለታቸው የማይመስል ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
ዘለንስኪ የቀድሞው ፐሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን የሚያነሱት ለምርጫ ግብአት እንጂ ከልባቸው አይደለም ካሉ በኋላ ፤ በ24 ሰዓት ጦርነቱን በማስቆም ሞስኮና ኬቭን ሰላም አደርጋለሁ ማለታቸው ከቃል ያለፈ ሀሳብ አይሆንም ሲሉ ከ CNN ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡
እንደ አር ቲ ዘገባ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት የሚለመለሱ ከሆነ ቀዳሚ ስራቸው የሞስኮና ኬቭን ጦርነት እስከወዲያኛው ማስቆም እንደሆነ በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ አልጀዚራ እንደዘገበው ደግሞ ሩሲያ በዩክሬን ሁለተኛዋ ግዙፍ ከተማ በሆነቸው ካርኪቭ በሚገኝ አፓርትመንት በፈጸመችው የቦምብ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 42 የሚሆኑ መቁሰላቸውን የዩክሬን ባለሰልጣናት አስታውቀዋል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












