፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 06 2017| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ በአዲስ አበባ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገለጸ።
ቢሮው የበዓላቱን አከባበር አስመልክቶ ከጸጥታና ደንብ ማስከበር መዋቅሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፤ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን በሰላም ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ለዚህም የሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የደንብ ማስከበር መዋቅሮች በዓሉ የህዝቦችን አብሮነት በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት የህዝቦች አብሮነትና የትብብር ምንጭ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው በድምቀትና በሰላም እንዲከበሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የጸጥታ ሃይሉ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ የተለመደውን እገዛና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












