፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 06 2017| NBC ETHIOPIA- በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳ ውኃ ከተማ ነዋሪዎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት የተሟላ ሕክምና ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀዋል።
የመድኃኒት እጥረት ችግር ከጊዜ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ታክመን መዳን አልቻልንም ብለዋል።
በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ታካሚዎች ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ መኾኑን ገልጸዋል። ገንዘብ የሌላቸው ታካሚዎች ደግሞ መድኃኒቱን ገዝተው ባለመጠቀማቸው ምክንያት ከበሽታቸው በፍጥነት ማገገም አለመቻላቸውን ያነሳሉ።

የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ጤና ጣቢያ ኀላፊ በላይነህ አድማሱ በጤና ጣቢያዎች በቂ የመድኃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ችግር እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል ።
ይኽ የሆነው ደግሞ በበጀት እጥረት እና ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት መንገዶች በመዘጋታቸው መኾኑን የተናገሩት ኀላፊው ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መኾኑን አንሰተዋል።

የገንዳ ውኃ ከተማ አስተዳደር ጤና ጣቢያ ለብዙ ሕዝብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በተለይ ወደ ከተማው የሚገቡ የጉልበት ሠራተኞች እና የተፈናቃይ ማኀበረሰብ ክፍሎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተቋሙ ከፍተኛ የኾነ የመድኃኒት እጥረት እንዲገጥመው ምክንያት ኾኖል ሲሉ ኀላፊው ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዮሴፍ ጉርባ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ተናገረዋል ዘገባው የአሚኮ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












