፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 07 2017| NBC ETHIOPIA- የፈረንሳይ ምክር ቤት የአፍሪካ ቀንድ ወዳጅነት ቡድን አባላት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአፍሪካ ጉልህ ሚና የምትጫወት ናት ሲሉ ገለፁ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በሴናተር ሂዩግ ሶሪ የተመራውን የፈረንሳይ ፓርላማ የአፍሪካ ቀንድ ወዳጅነት ቡድን አባላትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላቱ የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት ታሪካዊ እና ረጅም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑን በመግለጽ፤ፈረንሳይ በኢትዮጵያ በልማት ትብብር፣በባህል፣በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዙሪያ የምታደርገውን ተሳትፎ አድንቀዋል።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የምትገኝበት ቀጣና መልከዓ ምድራዊ እና ስትራቴጂካዊ አቀማመጡ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው በመሆኑ የበርካታ አካላትን ትኩረት የሳበ መሆኑን ለፓርላማ አባላቱ አስረድተዋል።
አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ካላት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እና እያደገ ከመጣው ምጣኔ ሀብቷ አኳያ ባሕር በር ወሳኝ በመሆኑ በሰጥቶ መቀበል መርህ በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት እያደረገችው ያለውን ጥረት አብራርተዋል።

በሶማሊያ ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ስምሪት በጥንቃቄ መታየት እንደሚገባው ለሴናተሮቹ ገልጸዋል።
የፓርላማ አባላቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአፍሪካ ጉልህ ሚና ያላት አገር መሆኗን በመግለጽ የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንደሚገባውም በውይይታቸው ላይ ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












