፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 30 2016| NBC ETHIOPIA-ለይፋዊ ጉብኝት በቱርክ አንካራ የገቡትን የግብፁን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይብ ኤርዶሃን የሞቀ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ነው የተሰማው፡፡
አልሲሲን የያዘው አውሮፕላን በቱርኩ ኤዘንቦጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ይደርጉለት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይብ ኤርዶሃን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸው ሃካን ሬዳንና ከአንካራ ከተማ ከንቲባ ቫሲን ሳሂን ጋ በመሆን ነው፡፡

ከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸውን አስከትለው አንካራ የገቡት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን ባደረጉት ንግግር ቅድሚያ ወደር የሌለው ደስታ ተሰምቶኛል ያሉት፡፡
ቱርክና ግብፅ በፈርጀ ብዙ ትብብር ዙሪያ በጋራ በመስራት ቆርጠው መቆማቸውን ገልፀዋል ዘገባው የአዘር ኒውስ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












