፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 27 2016| NBC ETHIOPIA-ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ወይዘሮ አስቴር ዘውዴን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው እያስመረቀ ያለው በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰተማራቸውን 8 ሺህ 524 ተማሪዎችን ሲሆን ከተመራቂዎቹ መካከል በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ 3 ሺህ 708፣ በሶስተኛ ዲግሪ 82፣ በስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ 62 የህክምና ዶክተሮች ይገኙበታል። ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች መካከልም 3 ሺህ 34ቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












