፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 18 2016| NBC ETHIOPIA- አንድ በርካታ መጠን ያለው ነዳጅ ዘይት የጫነች መርከብ በፊሊፒንስ የውሀ ክልል መስመጧ ተሰምቷል፡፡
የፊሊፒንስን ሠንደቅ አላማ የምታውለበልበዋ መርከብ የጫነችው የነዳጅ መጠን ከአንድ ሚሊዩን አራት መቶ ሺህ ሊትር በላይ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡

ለኢንደስትሪ ግብዓት የሚውለውን ነዳጅ የጫነችዋ መርከብ በማኒላ አቅራቢያ ስትሰምጥ በውስጧ ከነበሩት ሰዎች አስራ ስድስቱን ማትረፍ መቻሉንና አንድ ሰው ግን የደረሰበት መጥፋቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የፊሊፒንስ የትራንስፖርት ሚኒስትር በሰጡት ማብራሪያ በባህር ላይ የተነሳው ከባድ የንፋስ ወጀብ በመርከቧ ላይ ያጋጠመውን የነዳጅ መፍሰስ ችግር በጊዜው ለመቅረፍ እንዳይቻል መሰናክል ሆኗል ነው ያሉት፡፡
ዘገባው የፍራንስ 24 ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












