፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 18 2016| NBC ETHIOPIA-ባንኩ ያስተዋወቀው አዲሱ ሲቢኢ ብር ፕላስ የተሰኘው መተግበሪያ ቀድሞ በሲቢኢ ብር ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ተሻሽሎ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ በመርሃ ግብሩ ላይ የዲጂታል ባንኪንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።
ዘንድሮ ከተከናወነ የገንዘብ ዝውውር 71 በመቶ የሚሆነው በዲጂታል አማራጭ የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ሲቢኢ ብር ፕላስ የተሰኘው አዲሱ መተግበሪያ ማንኛውንም የአገልግሎት ክፍያ በቀላሉ ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በአንድ ጊዜ ለአምስት ሰዎች ለመላክ እንደሚያስችል ተነግሯል።
በ-አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












