፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 19 2016| NBC ETHIOPIA- በ2016 በጀት አመት 57.14 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት አመት እቅድን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫው በአለም አቀፍ ላይ ያሉት የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት እና እስራኤል ሃማስ ጦርነት ዘርፉን በብዙ እየፈተኑት ነው ተብሏል።

በተጨማሪ በአገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉት አለመረጋጋቶች ሌላኛው የዘርፉ ፈተና ሆኖ የቆየ ነው ተብሏል።
ድርጅቱ በ2016 ለማግኘት አቅዶ ከነበረው 51.6 ቢሊየን ብር 57.14 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ አስታውቋል።
ከታክስ በፊት 6.70 ቢሊየን ለማትረፍ ታቅዶ ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።በ2017 በጀት አመት የትርፍ መጠኑን ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ለማድረስ መታቀዱን በመግለጫው ተመላክቷል።
በ-ሔርሜላ ፍቃደ











