፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 21 2016| NBC ETHIOPIA-የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ ገልጸዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለሁሉም የምክር ቤቱ አባላት የፊሲካል ፌዴራሊዝም መሰረታዊ ጉዳዮችና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በሚል ርዕስ የአንድ ቀን ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡
አቶ ተረፈ አክለውም የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከማካሄዱ አስቀድሞ የምክር ቤቱ አራት ቋሚ ኮሚቴዎች ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከጉባኤው አጀንዳዎች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ መክረው ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳቦች ይዘው እንደሚቀርቡ ጠቅሰዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












