፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 07 2016| NBC ETHIOPIA-ጅማሮውን በዋሻ ላይ ያደረገው የስዕል ጥበብ በዘመናት ተቃኝቶ እየረቀቀ እና ይበልጡን እየተወደደ መዝለቅ የቻለ የጥበብ ውጤት ነው፡፡ ቴክኖሎጂ መልክ እና ቀለሙን ሳይለውጠው እና ሳያደበዝዘው በዘመን ተሸጋሪነት ዛሬም ታሪክን፣ ባህልን፣ የፈጠራ ውጤትን በቀለማት አዋህዶ እየተናገረ ይገኛል፡፡
ለዛሬም የጎላ የጥበብ አሻራ ያረፈባቸው እንዲሁም ዘመናትን ተሻገረው መዝለቅ ከቻሉ የዓለማችን ዝነኛ እና እጅን በአፍ የሚስጭኑ ከተባለላቸው ስዕላት መካከል የተወሰኑት ልናስቃኛችሁ ወደድን።
በቅድሚያ የምናገኘው በአያሌ ሙያዎቹ በሚታወሰው ጣሊያናዊው አርቲስት በሊዮናርዶ ዳቪንቺ የተሳለውን የሞናሊዛ ስዕልን ነው።ይህንን ስዕል ከህጻን እስከ አዋቂ አይቶት ወይም ስለስዕሉ ሲወራ ሰምቶት ማያውቅ የለም ቢባል ጥቂቱ ነው፡፡
ሊዮናርዶ ዳቪንቺ በቅንድብ አልባነት በምትታወቀው፣ በመሳቅና በመኮሳተር መሀል ሆና በተሳለችው ሥዕሉ ሞናኒዛ እጅጉኑ ይታወቃል።

በጎርጎርሳውያኑ ከ1503 እስከ 1519 ድረስ እንደተሳለ የሚነገርለት የሞናሊዛ ስዕል በዓለም ላይ በጣም ውዱ ሥዕል ብቻ ሳይሆን በብዛት የተጎበኘ፣ በርካታ ውይይቶች የተደረጉበት፣ ብዙዎች የፃፉለት፣ በበርካታ ቋንቋ የተሞዘቀለት እና የተመሰገነ የዓለማችን ድንቅ የስዕል ጥበብ ነው።
ስዕሉ በ77 ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ53ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በተወጠረ ሸራ ላይ የተሳለ ሲሆን፣ ከዓለማችን ውድ ስዕሎች መካከልም አንዱ ነው። በ1962 ለዚሁ ስዕል የ100 ሚሊየን ዶላር ኢንሹራንስ ተገብቶለታል። እ.ኤ.አ በ2018 ዋጋው ወደ 650 ሚሊየን ዶላር አድጓል። ይሄም በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ላይ ቀዳሚ ሆኖ እንዲሰፍር አድርጎታል።
የሞናሊዛ ስዕል ከፈረንሳይ ሪፐብሊክ እጅግ ውድ ከሆኑ ንብረቶች መካከል አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ሙዚየሞች አንዱ በሆነው በፓሪስ ሉቭር ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል።
በቀጣይ የምናገኘው የአለማችን እጅግ ታዋቂው እና ወዱ ስዕል ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የተካፈለውን የመጨረሻውን እራት መነሻ ተደርጎ የተሳለው ትልቅ የግድግዳ ሥዕል ነው።

ስእሉ ከሊዮናርዶ ዳቪንቺ ዝነኛ እና ታዋቂ ስራዎች መካከል ከሞናንዛ በመቀጠል የምናገኘው የስዕል ጥበብ የፈሰሰበት ነው።
በጎርጎሮሳውያኑ ከ1495 እስከ 1498 ጣሊያን በሚገኘው የሳንታ ማሪያ ዴሌ ግራዚ ገዳም እንደተሳለ ይነገርለታል። በ460ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ880ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት የሚለካ ሲሆን፣ በገዳሙ የሚገኘውን የመመገቢያ አዳራሽ አጠቃላይ ግድግዳን ይሸፍናል።
ሥዕሉ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አሳልፎት እንደሚሰጥ የተናገረበትን እና 12ቱ ደቀ መዛሙርት በተለያዩ ስሜቶች እና ገጽታዎች ያስመለክተናል።
ይህ ስዕል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአንዳንድ ጥቃቶች፣ በእርጥበት እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ጉዳት ቢደርስበትም ዛሬም ድረስ ከዳ ቪንቺ በጣም የተከበሩ እና የተጠኑ ስራዎች አንዱ ሆኖ ዘመናት መሻገር የቻለ ሆንዋል።
የሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ የመጨረሻው እራት ሥዕል በአሁኑ ጊዜ በሚላን ፣ ጣሊያን በሚገኘው የሳንታ ማሪያ ዴል ግራዚ ገዳም ሪፌቶሪ (የመመገቢያ አዳራሽ) ውስጥ ይገኛል።
በሆላንዳዊው አርቲስት ቪንሰንት ቫን ጎግ የተሳለው ‹‹ስታርሪ ናይት›› ሥዕል ሌላኛው የዓለማችን እውቁ የስዕል ጥበብ ስራ ነው።

ስታርሪ ናይት በጎርጎሮሳውያኑ በ1889 የተሳለ በፈረንሳይ ሴንት-ሬሚ በሚገኘውን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ ሆኖ በመስኮት በኩል ወደውጪ ያለውን እይታ የሚያስመለክት ስዕል ነው።
በሥዕሉ ላይ ተለዋዋጭ የሌሊት ሰማይ እና ጨረቃ ያሳያል። ስታርሪ ናይት ሥዕል ከቫን ጎግ ዝነኛ እና የተከበሩ ሥዕሎች አንዱ ነው።
ይህ ስዕል በ73 ሴሜ ሳ.ሜ የቁመት መጠንና በ92 ሴ.ሜ) ሳ.ሜ የአግድሞሽ ቁመት በሸራ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ ከ1941 ጀምሮ ለእይታ በቀረበበት በኒውዮርክ የዘመናዊ ጥበብ ሙዚየም (ሞኤምኤ) ዛሬም ለጎብኚዎች ክፍት እንደሆነ ነው።
እ.ኤ.አ. በ2017 አምስተርዳም የሚገኘው የቫን ጎግ ሙዚየም የስዕሉ ዋጋ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንሹራንስ ገብቶለታል።
ስታርሪ ናይት ቫን ጎግ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ጥልቅ ግንኙነት እና የተፈጥሮን አለም በጥልቅ ግላዊ እና መንፈሳዊ ፍቺው በኪነጥበብ የመሙላት ችሎታውን ያሳየበት ስዕሉ መሆኑን ይነገራል።
በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ታዋቂ የጥበብ ስራዎች አንዱ ነው።The Scream ይህ የዓለማችን ታዋቂ ስዕል በጎርጎሮሲያኑ በ1893 በኖርዌያዊው አርቲስት ኤድቫርድ ሙንች ተስሏል።
The Scream ቀይ ብርቱካንማ ሰማይ ላይ እጆቹን ጭንቅላቱ ላይ አደርጎ ከባድ ጩኸት የሚያሰማን ሰውን ያስመለክታል።

በዓለም ላይ ካሉ በጣም ውድ ሥዕሎች አንዱ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2012 በ 120 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጧዋል፡፡ ይህም በወቅቱ ከተሸጡ የጥበብ ስራዎች እጅግ ውዱ ነበር፡፡
ይህ የዓለማችን ታዋቂ ስዕል ከ1893 በኦስሎ, ኖርዌይ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል።
“ጉርኒካ” በስፔናዊው አርቲስት ፓብሎ ፒካሶ የተሳለ ሌላኛው የዓለማችን ታዋቂውን ዝነኛው የስዕል ጥበብ ነው።

በጎርጎሮሳውያኑ በ1937 በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በጊርኒካ ከተማ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት በ‹‹ፒካሶ›› ጥበብ ምላሽ የተሰጠበት ስለመሆኑ ይነገራል።
በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት በባስክ ክልል በጊርኒካ ከተማ ጀርመን የወሰደችውን የአየር ላይ የቦምብ ጥቃትን በመታሰቢያነት ያሰፈረው ሥዕሉ፣ ከ11 ጫማ በላይ ቁመት እና ከ25 ጫማ ስፋት አለው፡፡ በእያንዳንዱ የስዕሉ ቀለማት የጦርነትን አስፈሪነት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ የቀረበው እ.ኤ.አ በ1937 በስፔን ፓቪልዮን ሲሆን፣ ከዚያም በ1981 ማድሪድ በሚገኘው ሬና ሶፊያ ሙዚየም ውስጥ ከመቀመጡ በፊት ለ20 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ ተዘዋውሯል።
“ጉርኒካ” በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተሳሉ ስዕሎች የጦርነት ጭካኔዎችን በመቃወም ከተሰሩ የጥበብ ስራዎች በጉልህ ተቀምጧል፡፡
በ-ሃይማኖት ወርቁ